Monday, December 2, 2013

Awesome Things: A Mom is driving a little girl to her friends hous...

Awesome
Things: A Mom is driving a little girl to her friends
hous...
: A Mom is driving a little girl to her friends house
for a play date. “Mommy,” the little girl asks, “how old are you?” The
mother looks...

Tuesday, November 26, 2013

ገዳያችን ማነው? ድህነት ወይስ ኣረቦቹ? ድህነትና ኣረቦቹ እየተቀባበሉን በክብራችን ላይ እየቀለዱ እንደሆነ ይሰማኛል:: የዜጎቹ ሞት የማይቆረቁረው መንግስት፣ የወንድም እህቶቹን ሞት የ'ማንቼ' ድል የሚያስረሳው ትውልድ ባለባት ሃገር ላይ እየኖርኩ፣ በባእድ ሃገር ያሉ ወገኖቼ ሞት ቢያመኝም ኣይገርመኝም!! ችግራችን ሁሉ በድህነት ጀምሮ በድህነት ያበቃል፤ ገንዘብ በማጣት ጀምሮ ህይወትን በመገበር ይቁዋጫል:: 'ጥልያን መጣ' ብሎ ቆንጨራ... ጎራዴ... የሳለው ሀበሻ የዘመናት ወራሪውን ድህነትን ግን በጥቁር እንግዳ ደንብ ቡና ኣቀራርቦ የተቀበለው ይመሰላል... ይሄ ሊያመን ይገባል!! ለምን ተሰደድን? ድህነት! ከሃገራቸው በጊዜ ገደብ 'ውጡ' ሲሉ ለምን ኣመነታን? ድህነት! ዲቪ የሚደርሰው ለምን 'አንኩዋን ደስ ኣለህ' ይባላል? ድህነት!!! ይሄ የሳውዲ ግርግር ከሳምንት ወይም ከሁለት ሳምንት በሁዋላ ይረሳል.... እንደ ቤቲና ተስፋዬ ገብረኣብ ወሬ... ድህነታችን ግን ይቀጥላል:: ድህነት ከቀጠለ ደግሞ ሌላ ስቃይ፣ ሌላ ሞት ይከተላል... ደግሞም ሌላ የፌስቡክ ወከባ! እስቲ በነካ እጃችን ድህነት ላይም እንጩህ!! ድምፁን ኣጥፍቶ ለሚገድለን ኣይጮህም እንዴ? ...ካልሆነ ግን.... በከንቱ ጩሀን፣ ለበቀቀን ተከታዮቻችንም ጥሪት ሳይሆን ጩሀትና ሽንፈትን ኣውርሰን የምናልፍ ቀሽሞች እንዳንሆን:: by yonas angesom kidane