Thursday, January 16, 2014

★ በወንዱ አልፈርድም!!! ★ "የሆንሽ አመዳም ደነዝ ነገር ነሽ። እንዴት በልጁ አልፈርድም ትያለሽ አንቺ ሴት አይደለሽ ነው ወይስ ሴት አይደለሽም? ልጅቱ ትንሽ አታሳዝንሽም አንቺ አረብ አገር እየኖርሽ እዴት በሰው ትፈርጃለሽ በሷ ቦታ አንቺ ብቶኝስ? " ትናንት የደረሰኝ መልክት ነው። ልጅቷን አላውቃትም። መልክቷን በሰአቱ ስላላየውት መልስ አልሰጠዋትም። መልስ ሰጥቼ ባናግራትም እንደ አያያዟ አንግባባም። "ምክነያቷ" ትሉም ይሆናል የቻልኩትን ያህል አሳጥሬ ላውጋችሁ። የመጻፍ ችሎታው እደሌለኝ ተረድታችሁ ለመረዳት ያህል አንብቡልኝማ ። ነገሩ እንዲህ ነው፦ ሰሞኑን እዚሁ ፌስቡክ ላይ የተለያዩ የፍቅር ታሪኮች እየሰማን ነው። ታሪኩን የምታቀርብልን በሳውዲ ነዋሪ የሆነችውን Etsgi,ን ሳላመሰግን አላልፍም። በአብዛኛው ያስደመጠችን ታሪክ ተመሳሳይነት ያለው ከመሆኑም በላየይ ባለታሪኮቹ በአረብ አገራት ይሚገኑ ሴቶች ናቸው ።አንድ ወንድ ደግሞ ከወደ ጣሊያን። አሁን እኔ "በወንዱ አልፈርድም" ያልኩበትን እና የላይኛው መልክት እዲደርሰኝ ያረገውን ታሪክ ነጥለን እናውራበት። ለባለታሪኳ " ሚሚ "የሚል ስም እኛው እንስጣት እና እንቀጥል። ሚሚ በቤሩት 5 አመታትን አሳልፋለች። በዚ ቆይታዋ በፌስቡክ አንድ ወጣትን ተዋወቀች። አወሩ ተግባቡ መግባባታቸው ሲጸና ወደ WhatsApp & Skype አደገ ሲል ሲል ፍቅር ተጀመረ። 1፦2 ፦እየተባለ ወራቶች ተቆጥረው አመት ሞላቸው። እሱ እዛው እዳለች ከቤተሰቦቹጋ አስተዋወቃት።" ነይ ከአንቺ እርቆ መኖር አላስቻለኝም" እያለም ይወተውታት ነበር። ከተል አድርጎም አገሩላይ ካፌ መክፈት እደሚፈልግ ነገራት። (ክፈችልኝ ማለቱ አልተገለጸም) ይህንን የሰማች የሚሚ ጓደኛ "ካፌ ከምትከፍችለት እዚሁ አንቺጋ አምጭው " ትላትና እሱን ቤሩት ለማስገባት ብዙ ሙከራ ተደረገ ሊሳካ አልቻለም። ሚሚ ከፍቅረኛዋ (ፍቅረኛ ከተባለ) የፌስቡክ ፍቅሯጋ መከሩበት እና ብሩን ልትልክለት ወሰነች። ካፌው ሊከፈት አራት (4) አመት የደከመችበትን የላቧ ጠብታ የሆነውን ጥርቅም 80,000 (ሰማኒያ ሺ) ኢትዮጲያ ብር ላከችለት። ፍቅሯ በደረሰው ብር አነስተኛ ካፌ ከፈተ ። በተጨማሪም ስራ ማካኤጃ (ስላነሰው) 10,000 (አስር ሺ) የኢትዮጲያ ብር ላከችለት። በዚህም አልበቃ 9,000 ብር የሚገመት ኮምፕዩተር፣ ዘመናዊ የእጅ ስልክ በተለያየ ግዜ የምታገኘውን 2,000ም 1,000ም የላከችለት ተደማምሮ 10,000 የኢትዮጲያ ብር የላከችው ሚሚ ስለፍቅሯ ስትናገር "ቻት ስናደርግም ሆነ ስንደዋወል እክብካቤው ልዩ ነው " ትላለች። ታዲያ ይህ ልዩ ተከባካቢው ተፈቃሪ እንደተራኪዋ አጠራር (የፌስቡክ ሌባ) ይህን ሁሉ ብር ከላከች በኋላ ነበር አለምንም መንደርደሪያ «አልፈልግሽም» በሚል ቃል አርቃ ወደቆፈረችው ጉድጓድ ወረወራትና እሱ የድል ችቦውን ለኮሰ። ሚሚ አወዳደቋ ከፋ ተንኮታኮተች። ዛሬም ማገገም አልቻለችም። ፍቅሯን አጣች፣ተስፋዋ መከነ፣ዙሩያዋ ጨለመ ፣ብቸኝነት ዋጣት በወንድ ተበደልኩ ብላ ጮኸች ።የአመታት ድካሟ ሜዳ ቀረ ። ይሄንን ከሰማው በኋላ ነበር ከግርጌው የተሰማኝን እንዲ ያኖርኩት፦ (ታሪኩን ስላጋራሽን ተባረኪ! ከዚህም የባሰ ጉያቸው ታቅፈው ከወላጆቻቸው ይልቅ ወጣት ወንዶችን የሚጦሩ ብዙ ሴቶች አውቃለው። ባስደመጥሽን ታሪክ የልጁ ጥፋት አልታየኝም። በአንድ አመት የፍቅር ቆይታ ሊያውም በአካል ለማታውቀው ወንድ ከወላጆቿ አስበልጣ የዚህን ያህል መሆኗ የስዋ ድክመት ነው። በዝች ስጋት በወረራት አለም እየተኖረ በድምጽና በፎቶ ከንፎ እራስን ከሰጡ በኋላ ተበዳይ ነኝ ማለት ለምን?) ይህን በማለቴ ነው ከላይ ያስነበብኳችው ቅንጭብ ስድብ የደረሰኝ። ደነዞች ሰው ሁሉ የደነዘ ስለሚመስላቸው የሚናገሩት በደነዝኛ ነው ። እኔ ግን አሁንም እላለው ይሄ ታሪክ እውነት ከሆነ .... እኳን በአካል ሳይተዋወቁ ስንቶች ትዳር መስርተው፣ወልደው ልጆቻቸውን ለማሳደግ ከአገር ሲወጡ በባሎቻቸው የተካዱ ሚስቶች የሉም? በሚስቶቻቸው የተካዱስ ባሎች የሉም? ባለ ታሪኳ ይህንን ሳታቅ ሳትሰማ ቀርታ ነው? ሚሚ ከቁሳቁሱ ውጪ የላከችው ጥሬ ብር ከ 100,000 በላይ ነው። እና ይሄ ሁሉ ካላት ብሯን በኪሷ ፍቅሯን በልቧ ይዛ አገሯ ብትገባ አይቀልም? ""ነይ "ብሏትም ነበር። ታሪኩላይ እዳየነው "ላኪልኝ "ብሎ ብዙም አላስገደዳትም ። ስለወደደችው እና ለፍቅሯ ስትል ያረገችው ከሆነ ላፈቀሩት እኳን ብር ነፍስም ይሰጣል። የሚወዱትን ሰው ገበና ምንም ይሁን ምን አይወራም። አሁን በአደባባይ በደንብ ስደቢኝ የኔ .....ተውኩት ባክሽ!

                                                                                                            by mita nahom

No comments:

Post a Comment